ለሠላማችን ይህ ነው ተብሎ የማይገመት ትልቅ ዋጋ ተከፍሎበታል
እኛ ኢትዮጵያዊያን የእርስ በእርስ ግጭትንና ጦረነትን የምናውቀው በወሬና በሚዲያዎች ብቻ አይደለም፡፡ በተግባርም እንዳሳለፍነው የእርስ በእርስ ግጭቱና ጦርነቱ ብዙ ነገር አሳጥቶናል፡፡ ለዚህ ደግሞ ችግሩ ያላነኳኳው ቤት ያለሞኖሩን መጥቀስ ብቻ በቂ ነው፡፡ አኛ ግጭትንና ጦርነትን የምናውቀው በተግባር በተጨፈጨፉ ህጻናት፣ ወጣቶች፣ አረጋውያንና እናቶችም ጭምር ነው፡፡ በብዙዎቻችን ቤት ዛሬም ድረስ አሻራው አለ፡፡ በሀገር ደረጃም ለድህነታችንና ለኋላ ቀርነታችን ዋናው መንስኤ…


