የትንሳኤ በዓል እየሱስ ክርስቶስ በደሙ የሰው ልጆችን ከሀጢአት ለማንጻት ራሱን አሳልፎ በመሰጠት ወደር የማይገኝለት ፍቅሩን በመስቀል ላይ ገልፆ በሞቱ ለሰዉ ልጆች ሁሉ ምህረት ያስገኘበት እና ሞትንም ድል በመንሳት ከሞት የተነሳበት በዓል መሆኑን ኃላፊው በመልዕክታቸው ገልፀዋል።
ትንሳኤ የተስፋ፣ የእምነት እና የአዲስ ህይወት ጅማሮ ምልክት እንደመሆኑ ይህ በዓል በልባችን ሰላምን፣ በማህበረሰባችን አንድነትን፣ በሀገራችንም ብልጽግናና እድገትን ይዞ ይመጣ ዘንድ ኃላፊው መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።
በዓሉ የፍቅር፣ የሰላም፣ የይቅርታ፣ የምህረት፣ የመተሳሰብ፣ የመረዳዳትና የደስታ እንዲሆን ኃላፊው መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።
መልካም በዓል!
አቶ ብሩክ ወርቅነህ
የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ
ሚያዚያ 3/2018 ዓ.ም


