የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ብሩክ ወርቅነህ የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለክርስትና እምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
የትንሳኤ በዓል እየሱስ ክርስቶስ በደሙ የሰው ልጆችን ከሀጢአት ለማንጻት ራሱን አሳልፎ በመሰጠት ወደር የማይገኝለት ፍቅሩን በመስቀል ላይ ገልፆ በሞቱ ለሰዉ ልጆች ሁሉ ምህረት ያስገኘበት እና ሞትንም ድል በመንሳት ከሞት የተነሳበት በዓል መሆኑን ኃላፊው በመልዕክታቸው ገልፀዋል። ትንሳኤ የተስፋ፣ የእምነት እና የአዲስ ህይወት ጅማሮ ምልክት እንደመሆኑ ይህ በዓል በልባችን ሰላምን፣ በማህበረሰባችን አንድነትን፣ በሀገራችንም ብልጽግናና እድገትን ይዞ ይመጣ…


