መበልፀግ የተቀናጀ የማህበረሰብ ልማት ድርጅት ለተለያዩ ዘርፎች የሚያገለግሉ የቁሳቁስ ድጋፍ አበርክቷል።
የላይብረሪ መፀሀፍትና ሲዲ፣ ለአይን ምርመራ የሚያገለግል ግዙፍ የህክምና መሳሪያን ጨምሮር የተላያዩ የህክምና ቁሳቁሶች፣ የህፃናት አልባሳት፣ለእሳት አደጋ ተግባር የሚያገለግል አምቡላንስ እንዲሁም የእሳት አደጋ ሰራተኞች አልባሳት ድርጅቱ ካበረከታተቸው ድጋፎች ተጠቃሽ ናቸው።
በመድረኩ የደሬደዋ አስተዳደር ክቡር ከንተባ አቶ ከድር ጁሀር በጎነት ከምንም በላይ ለራስ መሆኑን ገልፀው በሀገር ውስጥም በውጭም የሚገኙ የድሬደዋ ወዳጆችና ተወላጆች እያበረከቱ ያለው የበጎ ተግባር ስራዎች የሚመሰገን መሆኑን አስረድተዋል።
መበልፀግ የተቀናጀ የማህበረሰብ ልማት ድረጅት የጀመረውን መሰል ድጋፎች ማጠናከር እንደሚገባው ሌሎች አገር በቀል የበጎ አድራጎት ድርጅቶችም በዚሁ መሰል ዘርፍ የበኩላቸውን ለማበርከት እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።
የመበልፀግ የተቀናጀ የማህበረሰብ ልማት ድረጅት የቦርድ አባልና መስራች አቶ ሾኪ አሊ ድርጅቱ ቀደም ሲል ወጥ ባልሆነ ምልኩ የሚደረጉ ድጋፎችን ይበልጥ አጠናክሮ በተቀናጀ መልኩ ለማስቀጠል እቅድ እንዳለው ገልፀዋል።
በተለይም ትምህርት ፣ጤናና ህፃናትን የሚደግፉ ስራዎችን በፈረንሳይ ካሉ የድሬደዋ ወዳጆችና ተወላጆች ጋር በቅንጅት እንደሚሰራም አቶ ሾኪ ጠቁመዋል።


