በአስተዳደሩ በጥራትና በፍጥነት እየተከናወነ የሚገኘው የኮሪደር ልማት ስራ ከውበት በዘለለ ለምግብነት የሚውሉ ተክሎችንና ፍራፍሬዎችን በማካተት የከተማ ግብርናን በስፋት እየተገበረ ይገኛል።
በዚህም በለንበርዋን አካባቢ በተከናወነውና በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በተመረቀው የኮሪደር ልማት ስራ ውስጥ በከተማ ግብርና ብርትኳን፣ ፓፓዬ፣ ሙዝ ፣ ቡናና ሎሚ ምርቶችን ማልማት ተችሏል።
በዚህም የከተማው ወጣቶች በአረንጓዴ ልማት፣ በጥበቃና በእንክብካቤ ሥራዎች ላይ በመሰማራት ቋሚ ገቢ እንዲያገኙ መንገድ ከፍቷል።
የድሬዳዋ የኮሪደር ልማት ሰው ተኮርና የነዋሪዎችን ህይወት በተጨባጭ የሚቀይር ሲሆን፤ ድሬን ፅዱ፣ ውብና ለነዋሪዎች ምቹ የማድረግ ዓላማን አንግቦ እየተተገበረም ይገኛል።


