ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ እና ከድሬዳዋ መምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጅ በተውጣጡ ከፍተኛ ባለሞያዎች የተዘጋጀው የ 6 ተኛ ክፍል አስተዳደራዊ ፈተናንም ከ 8 ሺህ 100 በላይ ተማሪዎች በመፈተን ላይ እንደሚገኙም የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ ሱልጣን አልዪ አስታውቀዋል።
ለ 6 ተኛ ክፍል አስተዳደራዊ ፈተናም የሚሆኑ ግብአቶች አስቀድመው ከመዘጋጀታቸውም በላይ የመምህራንንም አቅም ማጎልበት እንደተቻለና ኩረጃንም ለማስቀረት ዘርፈ-ብዙ የቅድመ-ዝግጅት ስራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውንም ነው አቶ ሱልጣን አልይ ያስታወቁት ።
ሴቶችን በትምህርት ከማብቃት ረገድም ባለፍት አመታት በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ የሆኑት አቶ አቡበከር አዶሽ ተናግረው በ 6 ተኛ ክፍል አስተዳደራዊ ፈተናም የሴት ተማሪዎች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑን እንደሆነና ከ 8 ሺህ 115 ተማሪዎች መካከልም 3 ሺህ 792 የሚሆኑ ሴት ተማሪዎች መሆኑን አቶ አቡበከር አዶሽ ተናግረዋል


