የ 2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ለሁለተኛ ጊዜ የ6 ተኛ ክፍል አስተዳደራዊ ፈተና በዛሬው እለት መሰጠት ተጀምሯል::
ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ እና ከድሬዳዋ መምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጅ በተውጣጡ ከፍተኛ ባለሞያዎች የተዘጋጀው የ 6 ተኛ ክፍል አስተዳደራዊ ፈተናንም ከ 8 ሺህ 100 በላይ ተማሪዎች በመፈተን ላይ እንደሚገኙም የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ ሱልጣን አልዪ አስታውቀዋል። ለ 6 ተኛ ክፍል አስተዳደራዊ ፈተናም የሚሆኑ ግብአቶች አስቀድመው ከመዘጋጀታቸውም በላይ የመምህራንንም አቅም ማጎልበት እንደተቻለና ኩረጃንም ለማስቀረት ዘርፈ-ብዙ የቅድመ-ዝግጅት…


