የድሬዳዋ የኮሪደር ልማት ለከተማዋ ውብ ገፅታን ከማላበሱ ባሻገር ለከተማ ግብርና እና ለሥራ ዕድል ፈጠራ ትልቅ በር ከፍቷል
በአስተዳደሩ በጥራትና በፍጥነት እየተከናወነ የሚገኘው የኮሪደር ልማት ስራ ከውበት በዘለለ ለምግብነት የሚውሉ ተክሎችንና ፍራፍሬዎችን በማካተት የከተማ ግብርናን በስፋት እየተገበረ ይገኛል። በዚህም በለንበርዋን አካባቢ በተከናወነውና በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በተመረቀው የኮሪደር ልማት ስራ ውስጥ በከተማ ግብርና ብርትኳን፣ ፓፓዬ፣ ሙዝ ፣ ቡናና ሎሚ ምርቶችን ማልማት ተችሏል። በዚህም የከተማው ወጣቶች በአረንጓዴ ልማት፣ በጥበቃና በእንክብካቤ ሥራዎች ላይ…


