ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ::
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው ናሬንድራ ሞዲ በሕንድ ታሪክ ለረጅም ጊዜ ያገለገሉ ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን ታሪካዊ ምዕራፍ ማስመዝገባቸውን ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማኅበራዊ ትስስር ገጽ ባስተላለፉት መልዕክት፤ “ታላቅ ወንድሜ እና ውድ ወዳጄ ክቡር ናሬንድራ ሞዲ፣ የዓለማችንን ትልቁን እና እጅግ ንቁ…


