ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ሥራን በይፋ አስጀመሩ::
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ሥራን የመሠረት ድንጋይ በማስቀመጥ በዛሬው ዕለት በይፋ አስጀምረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንኑ አስመልክቶ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጽ ባሰፈሩት መልዕክት፣ “የኢትዮጵያን ፈጣን የአየር ትራንስፖርት ዕድገት እና እየሰፋ የመጣውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዓለም አቀፍ ትሥሥር ዘላቂ ለማድረግ ወደ 25 ሚሊዮን የሚጠጉ መንገደኞችን በዓመት የማስተናገድ አቅሙ ላይ ከደረሰው ከአዲስ…


