ከደቡብ አፍሪካ ጁሀንስፐርግ፣ ከሩዋንዳ ኪጋሊ እንዲሁም ከኢንተርናሽናል ኢንስቲትዩት ፎር ሰስተነብል ዲቨሎፕመንት( international institute for Sustainable development) እና ወርልድ ሪሶርስ ኢንስቲትዩት WRI ( world resources institute) የተውጣጡ የስራ ኃላፊዎችና የመንግስት አካላት ልኡካን ቡድን በድሬዳዋ አስተዳደር ለአራት ተከታታይ ቀናት በሰንካሳ (SUNCASA) ፕሮጀክት በተሰሩ ስራዎች ላይ ሲያከናውን የቆየውን የልምድ ልውውጥጥ መድረክና ይፋዊ የስራ ጉብኝት በዛሬው እለት አጠናቀቀ።
ልዑክ ቡድኑ ማምሻውን የኮሪደር ልማት ስራዎችን ተዘዋውሮ ጎብኝቷል።
የልኡክ ቡድኑ አባላት የኮሪደር ልማቱ ለድሬዳዋ ማራኪ ገፅታን ከማላበሱ ባሻገር በልማቱ የተገነቡ ደረጃቸውን የጠበቁ የህዝብ መናፈሻዎችና መዝናኛ ስፍራዎች ለነዋሪዎች ምቾትን እንደፈጠሩ መመልከታቸውን ተናግረዋል።
የድሬዳዋ አስተዳደር የአካባቢ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ባለስልጣን የፕሮጀክቱ አስተባባሪ የሆኑት አቶ ደረጀ አቢቲ በበኩላቸው የአየር ንብረት ለውጥን ለመቀልበስ የተቀናጀ የገጠርና የከተማ የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃና መልሶ ማልማት ስራዎችን መስራት አስፈላጊ መሆኑን ተናግረው ሰንካሳ ፕሮጀክት እያከናወነ የሚገኘው ስራ ተስፋ ሰጪ እንደሆነና ከልምድ ልውውጡ መድረክ የተገኙ ሞክሮዎችን በቀጣይ የመተግበርርስ ሥራዎችን እንደመመሰሩ ተናግረዋል።


