የቁልቢ ገብርኤል የንግስ በዓልን ለማክበር የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ስራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ እንዲሁም የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሀፊ ብፅዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የሚመራ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን ብፁዓን አባቶች ቡድን ድሬዳዋ መግባታቸው ይታወቃል ።
ብፁዓን አባቶች በድሬዳዋ አስተዳደር በነበራቸው ቆይታ የአስተዳደሩ ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሀርን ጨምሮ ከፍተኛ የአስተዳደሩ አመራሮች ፣ የፖሊስ ኮሚሽን አመራሮች እና አባላቶች እንዲሁም የድሬዳዋ ሀገር ስብከት ሊቀ ፓፓስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፁህ አቡነ በርተሎሜዎስ እና የሀገረ ስብከት አባቶች ላደረጉላቸው ደማቅ አቀባበል እና መስተንግዶ በዛሬው እለት በተደረገላቸው የእራት ግብዣ ላይ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።


