ብፁዓን አባቶች በድሬዳዋ አስተዳደር ለተደረገላቸው አቀባበል እና መስተንግዶ ምስጋናቸውን አቀረቡ ።

የቁልቢ ገብርኤል የንግስ በዓልን ለማክበር የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ስራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ እንዲሁም የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሀፊ ብፅዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የሚመራ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን ብፁዓን አባቶች ቡድን ድሬዳዋ መግባታቸው ይታወቃል ። ብፁዓን አባቶች በድሬዳዋ አስተዳደር በነበራቸው ቆይታ የአስተዳደሩ ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሀርን ጨምሮ ከፍተኛ የአስተዳደሩ አመራሮች ፣ የፖሊስ ኮሚሽን አመራሮች እና አባላቶች…

Read More

ጤና ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጋር በመተባበር በዳሰነች ወረዳ በድሮን የታገዘ የክትባት ስርጭት በይፋ ጀመረ::

የጤና ሚኒስቴር ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢንሳ) ጋር በመተባበር፣ የማርበርግ ቫይረስ ስጋት ባለባቸው አካባቢዎች የህይወት አድን መድኃኒቶችንና ክትባቶችን በድሮን የማድረስ ስራ ዛሬ በይፋ ጀምሯል። ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የወረርሽኙን ስርጭት ለመግታትና ራቅ ያሉ አካባቢዎች የሚገኙ ዜጎችን ህይወት ለመታደግ በወሰደው የፈጣን ምላሽ እርምጃ፣ ዛሬ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በዳሰነች ወረዳ በድሮን የታገዘ የክትባት ስርጭት በስኬት ተከናውኗል። የዳሰነች ወረዳ…

Read More

የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የቅዱስ ገብርኤል ንግስ በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ምስጋና አቀረበ።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ዘንድ በአመት ሁለት ጊዜ በታላቅ ድምቀት የሚከበረው የቅዱስ ገብርኤል በዓለ ንግስ ያለ አንዳች የፀጥታ ችግር የትራፊክ አደጋ በሰላም ተከብሮ መጠናቀቁ ተገልፁዋል ። በአሉ በሰላም ተከብሮ መጠነቀቁን አስመልክቶ የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ክቡር ኮሚሽነር አለሙ መግራ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል። ኮሚሽነሩ በመግለጫቸው በዓሉ ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ተከብሮ እንዲያልፍ ለማስቻል የምስራቅ…

Read More

በድሬዳዋ አስተዳደር የቅዱስ ገብርኤል የንግስ በዓል በሳባ ደብረ ሀይል ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል ቤተክርስቲያን በድምቀት ተከበረ::

አመታዊውን የቁልቢ ገብርኤል የንግስ በዓል በዛሬው ዕለት በድሬዳዋ በርካታ ምእመናን በተገኙበት ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መልኩ ተከብሯል። የወረዳ 2 አስተዳደር ስራ አስፈጻሚ አቶ አቤል ምስራቅ በቀጠናው ካሉ ፖሊስ ጣቢያዎች ጋር በመቀናጀት እንዲሁም የእስልምና እምነት ተከታይ ከሆኑ እህት ወንድሞች ጋር በጋራ በመሆን ለበዓሉ ታዳሚዎች ማእድ ማጋራት እንደተከናወነ ጠቁመዋል። አቶ አቤል አያይዘውም ድሬዳዋ የአብሮነትና የፍቅር ከተማ መሆኗን ገልፀው፤…

Read More