የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የቅዱስ ገብርኤል ንግስ በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ምስጋና አቀረበ።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ዘንድ በአመት ሁለት ጊዜ በታላቅ ድምቀት የሚከበረው የቅዱስ ገብርኤል በዓለ ንግስ ያለ አንዳች የፀጥታ ችግር የትራፊክ አደጋ በሰላም ተከብሮ መጠናቀቁ ተገልፁዋል ።

በአሉ በሰላም ተከብሮ መጠነቀቁን አስመልክቶ የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ክቡር ኮሚሽነር አለሙ መግራ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

ኮሚሽነሩ በመግለጫቸው በዓሉ ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ተከብሮ እንዲያልፍ ለማስቻል የምስራቅ ኢትዮጵያ የፀጥታ አካላት ማለትም የምስራቅ ዕዝ ሀገር መከላከያ ፣የምስራቅ ምድብ ፌደራል ፈጥኖ ደራሽ ፖሊስ ፣የድሬዳዋ ፖሊስ፣ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ፣ የሚንሻ ኃይሉ እንዲሁም የአጎራባች ክልል የፖሊስ ኮሚሽኖች በጋራ የፀጥታ እቅድ በመውጣት አስቀድሞ ወደ ስራ መግባታቸውን ገልጸው በእቅዱ መሰረት ስራዎች በመከናወኑ በዓሉ ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ተከብሮ ማለፍ መቻሉን ተናግረዋል።

ክቡር ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ አክለውም በዓሉ በሰላም መጠናቀቅ የባለ ድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሰራር፣ የፖሊስ አመራር እና አባላት የፈጻሚነት ብቃት ጉልህ ሚና እንደነበረዉና በተለይ በእንግዳ ተቀባይነት የሚታወቀው የድሬዳዋ ህዝብ ወደ ድሬዳዋ የመጡ እንግዶች ፍቅር በተሞላበት ኢትዮጵያዊነት በሆነ መልኩ እንግዶችን በመቀበል በተለያዩ ወረዳዎች ላይም ድንኳኖችን በመጣል ፣ማዕድ በማጋራት ላከናወኑት ተግባራት እና በዓሉ ፍጹም ሰላማዊ ሆኖ ተከብሮ እንዲያልፍ በማስቻል ረገድ ከፖሊስ ጎን በመቆም ማህበረሰቡ ስላደረገው እገዛና ተሳትፎ ምስጋናቸውንም አቅርበዋል።

በዛሬው ዕለት በሳባ ደብረ ሃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ህዝበ ምዕመኑ በዐሉን አክብሮ ወደ ቤቱ ሲመለስ ለሊቱ የእኛ ነው በሚል መርህ የተለያዩ በጎ ተግባራትን የሚያከናውኑት የድሬዳዋ የሌሊት ታክሲ ማህበር ለበዓሉ ታዳሚ የነጻ ትራንስፖርት በመስጠት ለሳዩት የተለመደ የበጎ አድራጎት ስራዎች ኮሚሽነሩ ላቅ ያለ ምስጋናቸውን አቀርበዋል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *