ብፁዓን አባቶች በድሬዳዋ አስተዳደር ለተደረገላቸው አቀባበል እና መስተንግዶ ምስጋናቸውን አቀረቡ ።
የቁልቢ ገብርኤል የንግስ በዓልን ለማክበር የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ስራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ እንዲሁም የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሀፊ ብፅዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የሚመራ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን ብፁዓን አባቶች ቡድን ድሬዳዋ መግባታቸው ይታወቃል ። ብፁዓን አባቶች በድሬዳዋ አስተዳደር በነበራቸው ቆይታ የአስተዳደሩ ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሀርን ጨምሮ ከፍተኛ የአስተዳደሩ አመራሮች ፣ የፖሊስ ኮሚሽን አመራሮች እና አባላቶች…


