“ድሬዳዋ የአብሮነት፣ የፍቅርና እንግዳ ተቀባይ ከተማ መሆኗን በተግባር ተመልክተናል” ።:- የቁልቢ ገብርኤል በዓለ ንግስን ለማክበር ከተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች ወደ ድሬዳዋ የመጡ እንግዶች።
አመታዊውን የቁልቢ ገብርኤል የንግስ በአልን ለማክበር ከተለያዩ የአለም ሀገራት ብሎም በሀገራችን ከሚገኙ አካባቢዎች በርካታ ኪሎ ሜትርን አቋርጠው እንግዶች ወደ ድሬዳዋ እየመጡ ሲገኙ፤ በዛሬው እለት በአሉን ለመታደም ወደ ድሬዳዋ ለመጡ እንግዶች የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር፣ የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ዋና አዛዥ ኮሚሽነር አለሙ መግራ እንዲሁም በአስተዳደሩ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች በድሬዳዋ መግቢያ የገነት መናፈሻ…


