የ2018 ዓ.ም ምርጫ ፍትሀዊ ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ በሆነ መልኩ እንዲጠናቀቅ ሴቶች ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው ተገለፀ::

የድሬዳዋ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ የምርጫ 2018 ዓ.ም የንቅናቄ ማስጀመሪያ የጥያቄና መልስ ውድድር ማካሄድ ጀመረ።

በዚህም በመርሃ-ግብሩ የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የሴቶች ክንፍ ኃላፊ ወ/ሮ ሁክሚያ መሀመድ ብልፅግና ፓርቲ ሴቶችን ለማብቃት ልዩ ትኩረት ሰቶ እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረው፤ ሴቶች በፖለቲካዊ፣ በኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዘርፎች ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየተሰሩ የሚገኙ ስራዎችን በቀጣይ የማጠናከር ስራ እንደሚሰራ አመላክተዋል።

ምርጫ 2018 ፍትሀዊ ሰላማዊና ዲሞክሪያሳዊ በሆነ መልኩ እንዲጠናቀቅ ሴቶች ከፍተኛ ሚና እንዳላቸውም ወ/ሮ ሁክሚያ በመግለፅ በቀጣይም በየወረዳዎች ላይ የጥያቄና መልስ ውድድሩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቁመዋል።

የድሬዳዋ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ አይናለም መንገሻ በበኩላቸው የጥያቄና መልስ ውድድሩ ጥያቄዎች በዋነኝነት በብልፅግና ፓርቲ መተዳደሪያ ደንብ እንዲሁም በድሬዳዋ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ መተዳደሪያ ደንብ ዙሪያ ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።

የ2018 ዓ.ም ምርጫ ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ሴቶች ግንባር ቅደም ሆነው በመመረጥ፣በማስመረጥና በማስተባበር ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ወ/ሮ አይናለም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *