“ሠላም ለሁላችን” በሚል መሪ ቃል የሠላም የውይይትና ምክክር እንዲሁም የፀጥታ አካላት የምስጋናና ዕውቅና መድረክ በ05 ወረዳ ተካሔደ።
የድሬዳዋ ፓሊስ ጠቅላይ መምሪያ ዋና አዛዥ ኮሚሽነር አለሙ መግራ በመርሐግብሩ ላይ ተገኝተው እንደገለፁት ለሀገራችን ሠላም ባለቤቶች እራሳችን ስለሆንን ሁላችንም በያለንበት በባለቤትነት የጋራ የሆነውን ሠላም ማስጠበቅ እንደሚገባ ገልጸዋል።
በውይይቱ ላይ የተገኙት ወጣቶች እንደገር የተገኜውንና የመጣውን ሠላም በያገባኛል ስሜት ልንጠብቀው ይገባል በማለት ሀሳባቸውን አጋረተዋል።
የወረዳ05 ፀጥታ ማስተባበሪያ ሀላፊ አቶ ባንታለም ግርማ በበኩላቸው በወቅታዊ የወረዳው ሠላም ላይ የውይይት ሰነድ አቅርበዋል።
በመልካም ገጽታ የምትታወቀው ድሬዳዋን ለቁልቢ ገብርኤል ንግስ ባእል ወደከተማችን የሚመጡትን እንግዶች የንግዱ ማህበረሰብ እና የትራንስፓርት አገልግሎት የሚሰጡ የማህበረሠብ ክፍሎች በታማኝነትና በጥራት ሊያገለግሉ እንደሚባ ተመክሯል።
በአሰራርና በአመራር ብቃታቸው ላሳዮት ቁርጠኝነት ከወረዳ 05 አስተዳደር ለኮሚሽነር አለሙ መግራ ስጦታ ተበረክቶላቼዋል።
እንዲሁም ለአስተዳደሩ ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀርና ለአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች የእውቅና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።


