አመታዊውን የቁልቢ ገብርኤል የንግስ በአልን ለማክበር ከተለያዩ የአለም ሀገራት ብሎም በሀገራችን ከሚገኙ አካባቢዎች በርካታ ኪሎ ሜትርን አቋርጠው እንግዶች ወደ ድሬዳዋ እየመጡ ሲገኙ፤ በዛሬው እለት በአሉን ለመታደም ወደ ድሬዳዋ ለመጡ እንግዶች የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር፣ የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ዋና አዛዥ ኮሚሽነር አለሙ መግራ እንዲሁም በአስተዳደሩ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች በድሬዳዋ መግቢያ የገነት መናፈሻ ኬላ ላይ በመገኘት የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል አድርገዋል።
እንግዶቹ በአስተዳደሩ ለተደረገላቸው የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል መደሰታቸውን ገልፀው ድሬዳዋ የአብሮነት የፍቅርና እንግዳ ተቀባይ ከተማ መሆኗን በተግባር ተመልክተናል ሲሉ ተናግረዋል።
ድሬ ሁሌም የሰላም እና የአንድነት ከተማ ናት ያሉት እንግዶቹ በአስተዳደሩ ለተበረከተላቸው ጣፋጭ ምግቦች፣ ውሃ እና የተለያዩ አትክልትና ፍራፍሬዎች ምስጋናቸውን በማቅረብ “የእንግድነት ስሜታችን ጠፍቶ ሙሉ ለሙሉ የቤተሰባዊነት ስሜት ተሰምቶናል” ሲሉ ተናግረዋል።
የቁልቢ ገብርኤል በአልን ለማክበር ወደ ከተማችን ድሬዳዋ የሚመጡ እንግዶች ሰላማቸው ተጠብቆ ወደ መጡበት እስኪመለሱ ድረስ


