መጪዉ ታህሳስ 19 ቀን 2018 ዓ.ም የሚከበረዉ ዓመታዊ የቁልቢ ገብርኤል የንግስ በዓል ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲከበር በቂ ዝግጅት በማድረግ ወደ ስራ መግባቱ የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታዉቋል::
የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር አለሙ መግራ ለሚዲያ አካላት በበአሉ አከባበርና እንግዳ አቀባበል ዙሪያ መግለጫ ሰተዋል። ክቡር ኮሚሽነር አለሙ መግራ በመግለጫቸው በዓሉ ያለምንም የፀጥታ እና የትራፊክ አደጋ ችግር እንዲከበር ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር ረጅም ጊዜ የፈጀ ዝግጅት መደረጉን ገለፀው እንግዶችን ከመቀበል ጀምሮ የንግስ በዓሉ እስኪጠናቀቅ ድረስ የፀጥታ ኃይሉ በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡ በአሉን ለመታደም ከመላው የሀገራችን…


