የድሬዳዋ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን በሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ እና በደረሰኝ አጠቃቀም ዙሪያ ለአገልግሎት ሰጪ ተቋማት የግንዛቤ ማስጨበጫ የውይይት መድረክ በዛሬው እለት አካሂዷል።
በውይይት መደረኩ የድሬዳዋ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ዶ/ር አብድሰላም መሀመድ በወቅቱ እንዳሉት የውይይቱ መድረክ በዋናነት በመጪው ወራት የባእላት ወቅት እንደመሆኑ በርካታ ግብይቶች የሚፈጸሙበት እና ኢኮኖሚያዊ የሚጎለብትብት በመሆኑ የደረሰኝ አጠቃቀም ላይ ግብር ከፋዮ ግንዛቤውን ለማሳደግ ታስቦ የተዘጋጀ መድረክ መሆኑን ገልጸዋል።
ባለስልጣን መስሪያቤቱ በዋናነት ግብር ከፋዮን በማስተማር እና በማሰልጠን ህጉን ተከትለው እንዲሰሩ ለማስቻል ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ የንቅናቄ መድረኮችን እያካሄደ መሆኑን አንስተው ግብር ከፋዮ ህጉን ጠብቆ ያለመስራት መልሶ ግብር ከፋዮችን ሰለሚጎዳ ግብይታቸውን በህጉ መሰረት ሊያከናውኑ እንደሚገባም ኃላፊው አሳስበዋል፡፡
በመድረኩም የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ ምንነት፣ የማንዋል ደረሰኝ ምንነት፣ የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ የሚጠቀሙ ግብር ከፋዮች፣ የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ አጠቃቀም ጋር ተያይዞ ያሉ ዝርዝር ጉዳዮች በሰነድ ቀርቦ ሰፊ ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል።
የመድረኩ ተሳታፊዎችም በቀረበው ሰነድ ዙሪያ ጥያቄ እና አስተያየት ሰጥተው ውይይት ተደርጓባቸዋል።


