“የመጣውን ሁሉ ስንከተል ኋላ ቀርተናል፤ ይህ በመደመር መንግሥት ይቀየራል” – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ቴክኖሎጂ የተለዋዋጩ ምኅዳር ዘዋሪ በሆነበት በዚህ ወቅት ኢትዮጵያ ብሎም አፍሪካ በቂ የሚባል የተጠቃሚነት ድርሻን አላገኙም። ለዘመናት የተላመዱት የተቀባይነት ሚና በራስ ያለመቆምን የሚያለማምድ እና ሉዓላዊነትን የሚጎዳ ነው። በቴክኖሎጂ ውድድር ይህን ዕሳቤ ማራመድ እና ከሌሎች የተገዛ ሲስተም ተቀባይ ብቻ መሆን አዋጭ አለመሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል። ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ በዚህ ዕሳቤ እንደተጀመረ የገለጹት ጠቅላይ…


