በድሬዳዋ አስተዳደር በወረዳ 4 እና 5 እየተከናወኑ የሚገኙ የኮሪደር ልማት ስራዎች ለበርካታ ወጣቶች የስራ እድልን ፈጥረዋል።
በዚህም በወረዳዎቹ እየተሰሩ በሚገኙ የኮሪደር ልማት የስራዎች የስራ እድል ተፈጥሮላቸው ሲሰሩ ያነጋገርናቸው ወጣቶች የኮሪደር ልማቱ በሰፊው የስራ እድልን እንደፈጠረላቸው ገልፀዋል።
ስራውን በጥራትና በፍጥነት በተያዘለት የጊዜ ገደብ ለማጠናቀቅም በርብርብና በቅንጅት እየተሰራ እንደሚገኝም ወጣቶቹ አመላክተዋል።
የኮሪደር ልማት ስራው ከጊዜ ጋር ሊሄዱ የማይችሉ የግንባታ ስራዎችን በማስወገድ በአዲስና በዘመናዊ መልኩ በመገንባት ውብ ከተማን እየፈጠረ እንደሚገኝም አስተያየት ሰጪዎቹ ገልፀዋል።
እየተሰሩ የሚገኙ የኮሪደር ልማት ስራዎች የከተማዋን ገፅታ በመቀየርና ምቹ የስራ አካባቢን በመፍጠር ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳላቸው ወጣቶቹ ተናግረዋል።


