የሰው ሰራሽ አስተውሎትን በየዘርፉ መጠቀም እንደ አገር ያለውን እድገት ለማፋጠን እንደሚረዳ ተገለፀ።

በድሬደዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር የተማራ ልዑክ በኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጄንስ ኢኒስቲትዩት ጉብኝት አድረጓል።

በጉብኝቱ ክቡር ከንቲባ ከድር ጁሀር በድሬደዋ አስተዳደር ዘመናዊ አስተዳደርን በመዘርጋት ስማርት ሲቲን ለመፍጠር የሚያስችሉ ስራዎች እየተከናወነ መሆኑን ገልፀው ለአብነትም የመሶብ አንድ ማእከል አገልግሎት እንዲሁም በፍትህ ዘርፉ የተከናወኑ ተግባራትን ጠቅሰዋል።

በቀጣይም በሌሎች ዘርፎች ቴክኖሎጂን በተለይም ሰው ሰራሽ አስተውሎትን ለማስፋፋት እንደሚሰራ በዚህ እረገድ ከኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጄንስ ኢኒስቲትዩት ጋር በጋራ ለመስራት አስተዳደሩ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሞ ወደ ስራ መገባቱን ጠቅሰዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኅዳር 07/2018 ዓ.ም መርቀው ስራ ያስጀመሩት የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጄንስ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ይታገሱ ደሳለኝ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የልማት ሥራዎች የነገዋን ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት በሚያሳልጥ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ እንድትገኝ ያስቻለ እንደሆነ በወቅቱ ገልፀዋል።

ም/ል ዋና ዳይሬክተሩ በጉብኝቱ ላይ ኢትዮጵያ በዘርፉ በአፍሪካ ከፍ ያለ ስራ ለመስራት ምን እያከናወነች እንዳለች የሚያመላክቱ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን አካቶ የያዘ መሆኑን አብራርተዋል።

በጉብኝቱ በነበረው አጭር የውይይት ቆይታ በመስኩ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች መነሳሳት እንደ ፈጠረባቸው የጉብኝቱ ተሳታፊዎች ገልፀዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *