በድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር የተመራ የአስተዳደሩ አመራሮች ልዑክ በጅማ ከተማ ይፋዊ የስራ ጉብኝት እያካሄደ ይገኛል።
በድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃር የተመራው እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎችን ጨምሮ የዘጠኙም ከተማ ወረዳዎችንና የገጠር ክላስተር አመራሮችን የያዘ የልዑካን ቡድን ጅማ ከተማ ላይ ይፋዊ የስራ ጉብኝት በማካሄድ ላይ ይገኛል። በጅማ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት የአንድ መስኮት አገልግሎት አሰጣጥን ፣ በቢሮ ሪፎርም ትግበራ የተሰሩ ምቹ የስራ ከባቢን እንዲሁም የተገልጋይን እንግልት ለመቅረፍ በዲጂታል ስርዓት…


