በድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር የተመራ የአስተዳደሩ አመራሮች ልዑክ በጅማ ከተማ ይፋዊ የስራ ጉብኝት እያካሄደ ይገኛል።

በድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃር የተመራው እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎችን ጨምሮ የዘጠኙም ከተማ ወረዳዎችንና የገጠር ክላስተር አመራሮችን የያዘ የልዑካን ቡድን ጅማ ከተማ ላይ ይፋዊ የስራ ጉብኝት በማካሄድ ላይ ይገኛል።

በጅማ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት የአንድ መስኮት አገልግሎት አሰጣጥን ፣ በቢሮ ሪፎርም ትግበራ የተሰሩ ምቹ የስራ ከባቢን እንዲሁም የተገልጋይን እንግልት ለመቅረፍ በዲጂታል ስርዓት የታገዘ የአገልግሎት አሰጣጥን ልዑካኑ ተዘዋውረው ቃኝተዋል።

የጅማ ከተማ ከንቲባ አቶ ጠሃ ቀመር ለልዑካን ቡድኑ ዝርዝር ገለፃ እና ማብራሪያን የሰጡ ሲሆን ከለውጡ በፊት “ከተማ ሲያረጅ እንደ ጅማ” በሚል እሳቤ የሚገባትን ፀጋ አውጥታ እንዳትጠቀም ማነቆ የተጋረጠባት ከተማ ተደርጋ እንደነበር አስታውሰዋል።

ባለፉት ስድስት እና ሰባት አመታት በተሰሩ ስራዎች ተወዳዳሪ ከተማን ለመፍጠር እንደተቻለ ገልፀው የሁለቱን እህት ከተሞች ግንኙነት ለማጠናከር የድሬዳዋ አስተዳደር የሰጠውን ትኩረት አድንቀዋል።

የልዑካን ቡድኑ በጅማ ከተማ በሚኖረው ቆይታ በኮሪደር ልማት ስራዎች ፣ በቅርስ ጥበቃ እና እንክብካቤ ፣ በአምራች ኢንደስትሪ ዘርፎች ከተማዋ ያላትን ተሞክሮ የሚመለከት ይሆናል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *