“በኮሪደር ልማት ስራ አቧራን አራግፎ ከተማን ማስዋብ በመንግስት በጀት ብቻ የሚከናወን ሳይሆን በማህበረሰቡ ተሳትፎ መሆን እንዳለበት የጅማ ከተማ ተሞክሮ ማሳያ ነው” – ከንቲባ ከድር ጁሀር
በከንቲባ ከድር ጁሃር የተመራው እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎችን ጨምሮ የዘጠኙም ከተማ ወረዳዎችንና የገጠር ክላስተር አመራሮችን የያዘው የድሬዳዋ አስተዳደር የልዑካን ቡድን በጅማ ከተማ ጉብኝት አከናወነ። በጉብኝታቸውም የከተማዋን የወንዝ ዳር ተፋሰስ ልማት ሥራዎችን ፣ አምራች ኢንደስትሪዎችን ፣ ታሪካዊውን የአባ ጅፋር ቤተመንግስትን ጨምሮ የኮሪደር ልማት ስራዎችን ቃኝተዋል። በአምራች ኢንደስትሪ ዘርፎች እንዲሁም በስራ እድል ፈጠራ፥ የእንጨት ስራ ውጤቶች…


