ስነ-ምግባራዊና ቅንጅታዊ አሰራርን በማሳደግ የማህበረሰቡን እርካታ የሚጨምር አገልግሎት መስጠት እንደሚገባ ተጠቆመ::

የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ-ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በአስተዳደር ለሚገኙ ለሴክተር እና ትምህርት ተቋማት የሰው ሀብት ባለሞያዎች እና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች “ሙያዊ ስነ- ምግባር ለስነ-ምግባራዊ አገልግሎት አሠጣጥ እና ቅንጅታዊ አሰራር” በሚል ርዕሰ ስልጠና ሰቷል።

በዚህም በስልጠና መድረኩ የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ-ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ፌኑስ አብዱልጀባር ስልጠናው የስነ-ምግባር ብልሽቶችን ለመከላከል አቅም የሚፈጥር መሆኑን የተናገሩ ሲሆን፤ ለማህበረሰቡ የሚሰጡ አገልግሎቶች ከአድሎ በፀዳ መልኩ በኃላፊነት ሊሆን እንደሚገባ ተናግረዋል።

የሀገር እድገት የሚፋጠነው መልካም ስነ-ምግባርን ተላበሰው በሚሰሩ ዜጎች የጋራ ሕብረት መሆኑን ያመላከቱት ኮሚሽነር ፌኑስ ሙስና እና ብልሹ አሰራርን በመከላከል የሀገርን ልማት ለማፋጠን ሁሉም የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ ይገባል በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በመጨረሻም ኮሚሽነር ፌኑስ ስነ-ምግባራዊና ቅንጅታዊ አሰራርን በማሳደግ የማህበረሰቡን እርካታ የሚጨምር አገልግሎት መስጠት እንደሚገባ ጠቁመዋል።

የስልጠናው ተሳታፊዎች በበኩላቸው የስራ ላይ ስነ-ምግባር በመላበስ ከየትኛውም ሙስናና ብልሹ አሰራር በፀዳ መልኩ ለማህበረሰቡ አገልግሎት የመስጠት ሂደትን አጠናክረው እንደሚያስቀጥሉ ገልፀዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *