በድሬዳዋ አስተዳደር “ለአረጋውያን ደኅንነት እና መብቶች መጠበቅ ሁለንተናዊ ኃላፊነታችን እንወጣ” በሚል መሪ ቃል በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ35ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ለ34ኛ ጊዜ ዓለም አቀፍ የአረጋውያን ቀን የማጠቃለያ መርሃ-ግብር ተካሂዷል።
በዚህም በመርሃ-ግብሩ የድሬዳዋ አስተዳደር ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የሴቶች ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ፍሪ ጥበቡ ለበዓሉ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን በማስተላለፍ፤ አረጋውያን የሀገር ባለውለታ ለትውልድ አርዕያ የሚሆኑ በርካታ ስራዎችን የሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በአስተዳደሩ የአረጋውያንን ተጠቃሚነት ለማሳደግ በቁርጠኝነት እየተሰራ እንደሚገኝ የገለፁት ወ/ሮ ፍሪ አረጋውያንን መንከባከብ እና ያሉባቸውን ችግር መፍታት የሁሉም ማህበረሰብ ኃላፊነት መሆኑን አመላክተዋል።
የድሬዳዋ አስተዳደር አረጋውያን ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ ሀምዛ ዲላላ በበኩላቸው ጧሪ ያጡ አረጋውያንን የተመቻቸ ሁኔታ በመፍጠር ችግራቸውን በርብርብ መፍታት እንደሚገባ ገልፀዋል።
አቶ ሀምዛ አያይዘውም ማህበሩ ለአረጋውያን መብቶች መከበር እንዲሁም ተጠቃሚነታቸውን ለመጨመርና ተሳታፊነታቸውን ለማረጋገጥ እየሰራ እንደሚገኝ ጠቅሰው ስራዎች ውጤታማ እንዲሆኑ አስተዳደሩ እያበረከተው ለሚገኘው እገዛ አመስግነዋል።


