ታህሳስ 19 ቀን 2018 ዓ.ም የሚከበረው ዓመታዊ የቁልቢ ገብርኤል የንግስ በዓልን ለማክበር የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ስራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ እንዲሁም የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሀፊ ብፅዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የሚመራ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን ብፁዓን አባቶች ቡድን ድሬዳዋ ገብቷል።
እንግዶቹ በድሬዳዋ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ በድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር፣ በብፁዕ አቡነ በርተሎሜዎስ የድሬዳዋ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል እንዲሁም የሀገረ ስብከቱ የየመምሪያ ክፍል ኃላፊዎችና በአስተዳደሩ ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።


