በክቡር የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል የተመራ የፌደራል ፖሊስ ከፍተኛ አመራሮች ልኡክ ድሬዳዋ ከተማ ገባ::

ልዑኩ ድሬዳዋ ከተማ የገባው በድሬዳዋ እየተገነባ የሚገኘውን የመስራቅ ኢትዮጵያ ፈጥኖ ደራሽ ካንብ ግንባታን ለመጎብኘት እንዲሁም የሀረር ፖሊስ ሆስፒታል ማስፋፊያ ግንባታ ፕሮጀክትን የስራ ሂደት ለመመልከት መሆኑ ተገልጿል።

ልኡኩ ድሬዳዋ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ በድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር፣ በድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ዋና አዛዥ ክቡር ኮሚሽነር አለሙ መግራ እንዲሁም በአስተዳደሩ በሚገኙ ከፍተኛ አመራሮች ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *