የቅድስ ገብርኤል የንግስ በዓልን አስመልክቶ የወረዳ2 አስተዳደር የሙስሊሙ እህት ወንድሞች በሳባ ደብረ ሀይል ቅድስ ገብርኤል ካቴድራል ቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ በመገኘት የጽዳት ዘመቻ መርሃ ግብር አካሂደዋል።
የቅድስ ገብርኤል የንግስ በዓልን በድምቀት ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲከበር ለማድረግም አስተዳደርሩ በርካታ ስራዎች እየተከናወነ መሆኑን የገለጽት የወረዳ 2 አስተዳደር ስራ አስፈጻሚ አቶ አቤል ምስራቅ በወረዳው ከሚገኙ የጸጥታ አካል እንዲሁም የሙስሊም ማህበረሰብ በጋራ በዓሉን በደመቀ መልኩ እንዲከበር ለማድረግ የተለያዩ መርሀ ግብሮች በወረዳው መዘጋጀቱን ገልፀዋል።
በጽዳት ዘመቻው ሲሳተፉ ያገኘናቸው አካላትም ሲገልጹ ድሬዳዋ የሰላም የአብሮነት እርስ በእርስ በፍቅር በመተባበር የምንኖርበት ከተማ መሆኗን እና ይህንንም በተግባር የምንገልጥበት በዓል ነዉ ሲሉም ተናግረዋል።
በመርሃ ግብሩም ዓመታዊ የቁልቢ ገብርኤል የንግስ በዓልን ለማክበር የመጡ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ስራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ እንዲሁም የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሀፊ ብፅዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የሚመራ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን ብፁዓን አባቶች ተገኝተዋል።


