“በአስተዳደሩ ለሚገኙ አቅመ ደካመ ወገኖች የተከናወነው የቤት የግንባታ የማህበረሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ከፍተኛ አስተዋፆ አለው”። የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጋር በመተባበር በድሬዳዋ ያስገነባቸውን 20 ቤቶች ለአቅመ ደካማ ወገኖች አስተላልፏል።

በዚህም በርክክብ መርሃ-ግብሩ የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ለእንግዶች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸውን በማስተላለፍ የድሬዳዋ አስተዳደር በ 2017 ዓ.ም የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የኬኒያ ኤንባሲ ጋር በቅንጅት ለመስራት ካቀዳቸው ስራዎች መካከል አንዱ በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የአቅመ ደካሞች የመኖሪያ ቤት ግንባታ መረሃ- ግብር መሆኑን ጠቁመው የታቀዱ ስራዎች በስኬት መጠናቀቃቸውን አመላክተዋል።

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የኬኒያ ኤንባሲ

በአጭር ጊዜ ውስጥ 20 ምቹና ዘመናዊ የመኖሪያ ቤቶችን ለአቅመ ደካማ ወገኖች በሃያ ሚሊዮን ብር ገንብቶ ለምርቃት ማብቃቱንም ክቡር ከንቲባ ከድር ተናግረዋል።

ከንቲባ ከድር አያይዘውም በአስተዳደሩ ለሚገኙ አቅመ ደካመ ወገኖች የተከናወነው የቤት የግንባታ የማህበረሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ከፍተኛ አስተዋፆ እንዳለው በመጠቆም፤ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር) በበኩላቸው በአስተዳደሩ ለተደረገላቸው ደማቅ አቀባበል ምስጋናቸውን በማቅረብ በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተከናወኑ በሚገኙ የበጎ ፍቃድ ፍቃድ አገልግሎቶች በርካታ አቅመ ደካማ ወገኖችን ማገዝ እንደተቻለ አብራርተዋል።

የውጪ ጉዳይ ሚኒስትርና ተጠሪ ተቋማት ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት እንዲሁም ለድሬዳዋ ህዝብ ያለውን ፍቅር ለመግለፅ ለአቅመ ደካማ ቤተሰብ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ፣ የአረንጓዴ አሻራ እንዲሁም የቤት ግንባታና እድሳትን ጨምሮ የተለያዩ የበጎ ፍቃድ ተግባራት ማከናወኑን ገልፀዋል።

በመርሃ-ግብሩ የቤት ግንባታ ለተከናወነላቸው አቅመ ደካማ ወገኖች የቤት ቁሳቁስ እንዲሁም በ2 ሚሊዮን ብር የተገዙ የተማሪዎች የመማሪያ ቁሶችን በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ቤተሰብ ተማሪዎች ተበርክቷል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *