የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ብሩክ ወርቅነህ የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለክርስትና እምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የትንሳኤ በዓል እየሱስ ክርስቶስ በደሙ የሰው ልጆችን ከሀጢአት ለማንጻት ራሱን አሳልፎ በመሰጠት ወደር የማይገኝለት ፍቅሩን በመስቀል ላይ ገልፆ በሞቱ ለሰዉ ልጆች ሁሉ ምህረት ያስገኘበት እና ሞትንም ድል በመንሳት ከሞት የተነሳበት በዓል መሆኑን ኃላፊው በመልዕክታቸው ገልፀዋል። ትንሳኤ የተስፋ፣ የእምነት እና የአዲስ ህይወት ጅማሮ ምልክት እንደመሆኑ ይህ በዓል በልባችን ሰላምን፣ በማህበረሰባችን አንድነትን፣ በሀገራችንም ብልጽግናና እድገትን ይዞ ይመጣ…

Read More

የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ የትንሳኤ በአልን አስመልከቶ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ::

በዓሉ የሰላም ፣ የፍቅር ፣ የአንድነት እንዲሆን የተመኙት ክቡር ም/ከንቲባው ፤ ያለንን በማካፈል፣ ጐረቤትን በማገዝ እና በመጠየቅ እንዲሁም የተቸገሩትን በመርዳት በአሉን በጋራ ማሳለፍ እንደሚገባ በመልዕክታቸው ገልፀዋል። በዓሉ የፍቅር፣ የአብሮነት፣ የመተሳሰብ እና የመቻቻል እሴቶች ይበልጥ የሚጠናከሩበት ሊሆን እንደሚገባ ክቡር ም/ ከንቲባው ጠቁመው፤ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች የፍቅር፣ የሰላም፣ የደስታ፣ የብልፅግና እና የመተሳሰብ በአል ይሆን ዘንድ መልካም…

Read More

የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ::

በመልዕክታቸውም ለመላው የክርስትና ዕምነት ተከታዮች እንኳን ለትንሳኤ በዓል በሠላም፣ በአንድነትና በፍቅር አደረሳችሁ ብለዋል፡፡ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች በዓልን ደስተኛ ሆነው እንዲያሳልፉ ካለን ላይ በማካፈልና እርስ በእርስ በመረዳዳት እንዲሁም በመተሳሰብና በፍቅር በዓሉን ማሳለፍ እንደሚገባ ክቡር ከንቲባ በመልዕክታቸው ጠቅሰዋል። በመጨረሻም በዓሉ የሠላም፣ የደስታ፣ የፍቅር እንዲሆን እምኛለሁ በማለት ክቡር ከንቲባው የመልካም ምኞት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

Read More