በመልዕክታቸውም ለመላው የክርስትና ዕምነት ተከታዮች እንኳን ለትንሳኤ በዓል በሠላም፣ በአንድነትና በፍቅር አደረሳችሁ ብለዋል፡፡
ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች በዓልን ደስተኛ ሆነው እንዲያሳልፉ ካለን ላይ በማካፈልና እርስ በእርስ በመረዳዳት እንዲሁም በመተሳሰብና በፍቅር በዓሉን ማሳለፍ እንደሚገባ ክቡር ከንቲባ በመልዕክታቸው ጠቅሰዋል።
በመጨረሻም በዓሉ የሠላም፣ የደስታ፣ የፍቅር እንዲሆን እምኛለሁ በማለት ክቡር ከንቲባው የመልካም ምኞት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡


