በድሬዳዋ አስተዳደር ስምንተኛ ዓመትን የሚዘክር ደማቅ የህዝባዊ ድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ይገኛል
መጋቢት 24 ቀን የተጀመረውን ሀገራዊ የለውጥ ጉዞ ስምንተኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ፣ በዛሬው ዕለት በድሬዳዋ አስተዳደር ለገሀር አደባባይ ደማቅ የህዝባዊ ድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ይገኛል።
በመርሃ-ግብሩ የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ክቡር አቶ አብዲ ሙክታር፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ፣ የካብኔ አባላት የአስተዳደሩ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች፣ በርካታ ቁጥር ያላቸው የድሬዳዋ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።


