በዘንድሮው የመጀመሪያ ሩብ አመት በድሬደዋ አስተዳደር በመንገድ ላይ የትራፊክ አደጋ ሳቢያ በሰውና በንብረት ላይ ይደርስ የነበረውን የሞትና የንብረት ውድመት በከፍተኛ ደረጃ መቀነስ መቻሉን በፖሊስ ኮሚሽን የመንገድ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት አስታወቀ፡፡
ህግን በሚተላለፉ አሽከርካሪዎች ላይ የሚወሰደው እርምጃ በህብረተሰቡ ሊታገዝ ይገባል ተብሏል፡፡ ፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን በቅርቡ ባወጣው መረጃ በድሬደዋ አስተዳደር ያለው የተሸከርካሪ አሀዝ ከ25 ሺበላይ ስለመሆኑ ይነገራል፡፡ ታድያ በአስተዳደሩ ከተሸከርካሪ መበራከቱ ጋር ተያይዞ በያመቱ በሰውና ህይወትና ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ይከሰታል፡፡ የድሬደዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን የመንገድ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬትም በያዝነው አመት በከተማዋ የሚደርሱ የመንገድ ላይ የትራፊክ አደጋን…


