ህግን በሚተላለፉ አሽከርካሪዎች ላይ የሚወሰደው እርምጃ በህብረተሰቡ ሊታገዝ ይገባል ተብሏል፡፡
ፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን በቅርቡ ባወጣው መረጃ በድሬደዋ አስተዳደር ያለው የተሸከርካሪ አሀዝ ከ25 ሺበላይ ስለመሆኑ ይነገራል፡፡
ታድያ በአስተዳደሩ ከተሸከርካሪ መበራከቱ ጋር ተያይዞ በያመቱ በሰውና ህይወትና ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ይከሰታል፡፡
የድሬደዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን የመንገድ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬትም በያዝነው አመት በከተማዋ የሚደርሱ የመንገድ ላይ የትራፊክ አደጋን በከፍተኛ ደረጃ ለመቀነስ ስትራቴጂዎችን ነድፌ እየተንቀሳቀስኩ እገኛለው ብሏል፡፡
በዳይሬክቶሬቱ የመንገድ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክተር የሆኑት ኢንስፔክተር ይሔነው ሽፈራው እንደገለፁት በያመቱ በትራፊክ አደጋ ሳቢያ ሚነገሩ አሀዞችን ሪፖርት ከማድረግ በዘለለ አደጋው በምን ይደርሳል፤ መንስኤና መፍትሄው ብለን በመለየት አሁን ላይ ከፌደራል መንገድ ትራንስፖርት ባለስልጣን ድሬደዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ጋር በመቀናጀት ሰፊ የክትትልና ቁጥጥር ስራን እየሰራን እንገኛለን በዚህም በሩብ አመቱ ብቻ 4675 ህግ የተላለፉ አሽከርካሪዎችን በመቅጣት ከ1.2ሚሊየን ብር በላ ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ሁኗል ብለዋል፡፡
ህግን ላስከበር ቅጣት መፍትሄ ይሆናል ወይ አሽከርካሪው ቅጣቱ ተጋኗል ይላል ብለን ላነሳንላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽም እኛ ህግን በማስከበር አደጋን መቀነስን አላማ አርገን እየሰራን እንገኛለን ቅታቱም ቢሆን በህጉ የተቀመጠውን ነው እያስተገበርን ያለነው ብለዋል፡፡
በተደረገው ሰፊ የቁጥጥር ስራም አደጋ በከፍተኛ ደረጃ መቀነሱን ጠቁመው በመንገድ ላይ የትራፊክ አደጋ በ2012 በጥቅምት ወር ብቻ 4 ሰው ማለፉን አስታውሰው በዘንድሮው አመት ግን ሞት አለመመዝገቡን ተናግረዋል፡፡በቀጣይም የቁጥጥር ስራው ይጠናከራልም ብለዋል፡፡
ሌላው ማንኛውም አሽከርካሪ በትራፊክ ፖሊሶች ሳቢያ ቅሬታ ቢኖርበት በግልፅ ቅሬታውን ማቅረብ እንደሚችልም ጠቁመዋል፡፡
ማህበረሰቡም ከታሪፍ በላይ ከፍያን ሲጠየቅ ለሚመለከተው የህግ አካላት ሊያሳውቅ አሽከርካሪውም ህጉን ባግባቡ በመተግበር ካላስፈላጊ ቅጣት እንዲድንም ጥሪ አቅርበዋል፡፡


