በአስተዳደሩ ነገ ህዳር 5 የሚለገሰዉን ደም በአግባቡ ለመሰብሰብ ዝግጅት መጠናቀቁ ተገለፀ::

    በሀገራችን የተከሰተዉን ግጭት ተከትሎ የመከላከያ ሰራዊታችን የደም እጥረት እንዳያጋጥም ታስቦ ህዳር 5 /2013 ዓ.ም “ደሜን ለመከላከያ ሰራዊታችን እለግሳለሁ” በሚል መሪ ቃል የደም ልገሳ ስነ ስርአት ይካሄዳል።
    በመከላከያ ሰራዊታችን ላይ የደረሰውን ድንገተኛ ጥቃት ተከትሎ በደም እጥረት ምክኒያት የሚከሰት ሞትን ለማስቀረት የድሬ ደዋ ነዋሪ የሆኑ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በሚሳተፉበት የደም ልገሳ ስነስርዓት ላይ የሚለገሰዉን ደም በአግባቡ ለመሰብሰብ ዝግጅት መጠናቀቁ የድሬ ደዋ ጤና ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ለምለም በዛብህ ገለፁ፡፡
    በድሬ ደዋ በተለያዩ አከባቢዎች በሚደረገዉ የደም ልገሳ ስነስርዓት የሚሰበሰበዉን ደም በተገቢዉ መንገድ ተንከባክበዉ በመያዝ በአስተዳደራችን ብሎም በሀገራችን ለመከላከያ ሰራዊታችን አባላት እንዲሁም በተለያዩ ምክንያቶች የደም እጥረት ለሚያጋጥማቸዉ የህብረተሰብ ክፍሎች ደሙ እስኪደርስ ድረስ አስፈላጊዉ የህክምና እንክብካቤ እየተደረገለት ለማድረስ የሚያስፈልጉ ግብዓቶች ተሟላተዉ ስነስርዓቱን በመጠባበቅ ላይ መሆናቸዉንም ወ/ሮ ለምለም አብራርተዉ ሁለም የህብረተሰባችን ክፍሎች በተለይም ወጣቶች ወገኑ ለወገኖቹ ከሚሰጠዉ ስጦታዎች ሁሉ የላቀ ስጦታ የሆነዉን የደም ልገሳ ስነስርዓት ላይ በመሳተፍ የህልና እርካታ እና የዚህ ታሪክ ባለቤት እንዲሆኑ በማለት ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡