በ2012 ዓ.ም በድሬ ዳዋ የተከሰቱ ዋና ዋና አደጋዎችን ጉዳቶችን ለመቀነስ በተደረገው ርብርብ ላይ የህብረተሰቡ ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ

    በ2012 ዓ.ም በድሬ ዳዋ ከተከሰቱ ዋና ዋና አደጋዎችን መካከል 4 የተፈጥሮ አደጋዎች ድርቅ፣ ጎርፍ፣ ኮሮናና የአንበጣ መንጋ ሰዉ ሰራሽ አደጋ ግጭት፣መሆናቸውን ዛሬ ድሬዳዋ አስተዳደር አደጋ ስጋት ስራ አመራር ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የተከናወኑ ስራዎችና ቀጣይ እቅዶች ላይ በማተኮር ባካሄደው የምክክር መድረክ ላይ የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ሀርቢ ቡህ ገለፁ
    አክለዉም በ2013 ዓ.ም በተፈጥሮ እንዲሁም በሰው ሰራሽ የሚፈጠሩ አደጋዎች ትኩረት ለመስራት የያዙትን የ2013 እቅድ ዘርዘር ተደርገው የቀረቡ ሲሆን የቀረቡ ሰነዶችን መነሻ በማድረግ ሰፊ ውይይት ተደርጎ የመፍትሔ ሀሳቦች በተሳታፊዎች ተነስቷል።
    መድረኩን በንግግር የከፈቱት የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ ባደረጉት ንግግር በተፈጥሮም ሆነ በሰው ሰራሽ የሚፈጠሩ አደጋዎች አቅማችን አሟጠን እንዲሁም ከተቀናጀን የማንወጣው አደጋ ስለሌለ ሁሉም ሊረባርብ ይገባል ብለዋል ፡፡
    በጽ/ቤቱ የተከናወኑ የ2012 አፈጻጸም እና የ2013 እቅድ ዘርዘር ተደርገው የቀረቡ ሲሆን የቀረቡ ሰነዶችን መነሻ በማድረግ ሰፊ ውይይት ተደርጎ የመፍትሔ ሀሳቦች በተሳታፊዎች ተነስቷል።
    በተፈጥሮ እንዲሁም በሰው ሰራሽ የሚፈጠሩ አደጋዎች ትኩረት ተሰጥተውበት ዘላቂ መፍትሄ ቢሰጥ፣ የሚሰሩ ስራዎች በሚዲያ ቢደገፉ የሚሉ ሀሳቦች እና ሌሎችም ከተሳታፊዎች ቀርበዋል።
    ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ጠንካራ እቅድ በማቀድ ለሚፈጠሩ ችግሮች በተሟላ አቅም መሰራት እንዳለበትና ሁሉም የሚመለከታቸው አካላት የድጋፍ ርብርብ የሚፈልግ ጉዳይ መሆኑ እና በተፈጥሮም ሆነ በሰው ሰራሽ የሚፈጠሩ አደጋዎች አቅማችን አሟጠን እንዲሁም ከተቀናጀን የማንወጣው አደጋ አይኖርም በማለት በቀጣይ የጽ/ቤቱ መሰረታዊ ችግሮቹ ተፈትሸው ወደ ስራ የሚገባ መሆኑም ተገልጿል።