በምስራቁ የሀገሪቱ ክፍል ያለው የቁጠባ ባህል እንዲጎለብት በተለያዩ መንገዶች በሰራሁት ስራ ከ1.2 ሚሊየን በላይ ደንበኞችን ማፍራት አስችሎኛል አለ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምስራቅ ዲስትሪክ፡፡ ባንኩ የ7ኛው ዙር የይቆጥቡ ይሸለሙ ባለእድለኞችን ሸልሟል፡፡
ወጣት ናትናኤል ሁነኛው በሶማሌ ክልል ጎዴ ከተማ የመንግስት ሰራተኛ ሲሆን ከእለት ገቢው ላይ በቆጠባት አነስተኛ ገንዘብ በደረሰው እጣ መለስተኛ የህዝብ ማመላለሻ ተሸከርካሪ ተሸላሚ ሆኗል ወጣቱ እንደሚለው ሁሉም ማህበረሰብ ከገቢው ላይ የመቆጠብ ባህል ሊኖረው ይገባል፡፡
ሌሎች የባንኩ ተሸላሚዎች መሰል የሽልማት ፕሮግራሞች ለቁጠባ ባህል መጎልበት ሰፊ ድርሻ አላቸው ነው ያሉት፡፡ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የምስራቅ ዲስትሪክት የኦፕሬሽንና ሌጂስቲክ ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ኤልሳቤት ገብሩ የደንበኞች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ በመጨመር ላይ እንዳለና ማህበረሰቡን የቁጠባ ባህል ለማሳደግ በተሰራው ስራ ውጤት መምጣቱን ይገልጻሉ፡፡
የባንኩ የተቀማጭ ሂሳብ ከእጥፍ በላይ እድገት ማሳየቱን በመጠቆም ሌላው በጥቁር ገበያ ላይ ተሰፋፍቶ የነበረውና የባንኩን ህልውና ተፈታትኖት የቆየው የውጭ ምንዛሬ እጥረትም ከጠቅላይ ሚኒስትሩ የማስተማር ሂደት በኋላ ከፍተኛ ለውጥና እድገት ማሳየቱን ጠቁመዋል፡፡ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የምስራቅ ዲስትሪክት የቅርንጫፍ ብዛት ከ92 በላይ ሲደርስ የባንኩ ተቀማጭም 13 ቢሊየን ብር በላይ ሆኗል፡፡


