ከድሬዳዋ አስተዳደር እና ከድሬዳዋ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የተሰጠ መግለጫ.

    ትላንት ማታ በምዕራብ ወለጋ ዞን ጉሊሶ ወረዳ በንፁሃን ዜጎች ላይ በደረሰው እጅግ አሰቃቂ የወገን ህይወት መጥፋት የድሬዳዋ አስተዳደር፣ የድሬዳዋ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት እና ነዋሪዎች እጅጉን አዝነናል፤ በሰላማዊና ንፁሃን ዜጎች ላይ በደረሰው አረመኔያዊና ዘግናኝ ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት ልባችንም ክፉኛ ተሰብሯል፡፡ እኛ ኢትዮጵያዊያኖች ጠላት ያልደፈረን፤ ሰብዓዊ ክብራችንን ያላሳጣን ህዝቦች ሆነን ሳለ በየጊዜው በአካባቢና በማንነት ላይ ያተኮረ እጅግ ዘግናኝና…

    Read More

      የኮሮና ቫይረስን ከመከላከልና ከመቆጣጠር አንጻር የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሙሉካ መሐመድ እንደተናገሩት በአለም አቀፍ ወረርሽኝ COVID 19 ምክንያት ተቋርጦ የነበረውን ትምህርት ለማስቀጠልና ህፃናት የሚደርስባቸውን ስነ-ልቦናዊ ችግር ለመቅረፍ ትኩረት ተሰቶ እየተሰራ መሆኑን ገልፀው በየደረጃው በመሰራቱ የትምህርት ሂደቱ በመጀመሩ ውጤታማ የመማር ማስተማር ሂደትን ከማስፈን አኳያ አቅመ ደካማ ለሆኑ ተማሪዎች እየተደረገ የሚገኘው የቁሳቁስ ድጋፍ አመርቂ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

      እየተደረገ የሚገኘው ጥሩ ምሳሌ ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡ የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ እስቂያስ ታፈሰ በወቅቱ ባስተላለፉት መልዕክት እንደተናገሩት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በሌሎች መስኮች ላይ ካሳደረው ተፅዕኖ በተለየ መልኩ በትምህርት ዘርፍ ላይ የፈጠረው ችግር ጉልህ መሆኑን ጠቅሰው የቫይረሱን ስርጭት ከመከላከል አንጻር በአሁን ወቅት የሚስተዋለው መዘናጋት አሰቃቂ በመሆኑ ወላጆች ታዳጊ ህፃናት ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ኃላፊነት…

      Read More

        የድሬዳዋ ልጆችና ወዳጆች አለም አቀፍ ማህበር በድሬዳዋ ከተማ ድጋፍ አደረገ::

        የድሬዳዋ ልጆችና ወዳጆች አለም አቀፍ ማህበር በድሬዳዋ ከተማ በተለያዩ ትምህርት ቤቶች ከ250 ሺ ብር በላይ የሚገመት የትምህርት መርጃ ቁሳቁስና የገንዘብ ድጋፍ አደረጉ፡፡ በድጋፉ ላይ የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ ከድር ጀዋር እንደገለፁት በአስተዳደሩ ድጋፍ ለሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎች በተለያዩ መስኮች እየተደረገ የሚገኘው የመተጋገዝ ስራ የድሬዳዋን የመቻቻልና የፍቅር ከተማ ስያሜ የሚያጎላ…

        Read More