እየተደረገ የሚገኘው ጥሩ ምሳሌ ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡
የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ እስቂያስ ታፈሰ በወቅቱ ባስተላለፉት መልዕክት እንደተናገሩት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በሌሎች መስኮች ላይ ካሳደረው ተፅዕኖ በተለየ መልኩ በትምህርት ዘርፍ ላይ የፈጠረው ችግር ጉልህ መሆኑን ጠቅሰው የቫይረሱን ስርጭት ከመከላከል አንጻር በአሁን ወቅት የሚስተዋለው መዘናጋት አሰቃቂ በመሆኑ ወላጆች ታዳጊ ህፃናት ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ኃላፊነት እንዳለባቸው ገልፀዋል፡፡
ድጋፍ ከተደረገላቸው ህፃናት መካከል በተለይ የ12ኛ ክፍል ተማሪ የሆነችው እና በግላኮማ በሽታ ምክንያት ትምህርቷ ላይ ተፅዕኖ ያሳደረባት ተማሪ በማህበሩ የህክምና ወጪ የተሸፈነላት ሲሆን ሌሎች ህፃናትም በተደረገላቸው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡


