የአስተዳደሩ ፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ቢሮ የመልካም አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በተመረጡ አራት የመንግስት አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ላይ ከሚዲያ ጋር በመቀናጀት ድንገታዊ ምልከታ አድርጓል፡፡
በአስተዳደሩ ከፍተኛ ተገልጋይን ከሚያስተናግዱና የህዝብ ሮሮ በስፋት ከሚነሳባቸው ተቋማት መካከል በሁለት የቀበሌና በሁለት መንግስታዊ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ላይ የአስተዳደሩ ፐብሊክ ሰርቪስ እና ሰው ሀብት ልማት ቢሮ የመልካም አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በአስተዳደሩ ከሚገኙ ሚዲያዎች ጋር በመሆን ድንገታዊ ምልከታን አድርጓል፡፡
በዚሁ በፌደራል መንገድ ትራንስፖርት ባለስልጣን ድሬደዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተጀመረው ምልከታ ላይ ተገልጋዮች በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ በሚስተዋሉ መጓተቶችና አሽከርካሪውን አቅም ያላገናዘበ ቅጣትና፤ የታፔላ አሰጣጥ እንዲሁም በታክሲ አሽከርካሪዎች የሚነሳው የፈረቃ ይነሳልን ጥያቄ ለቡድኑ ከቀረቡ ጥያቄዎች ውስጥ ይገኙበታል፡፡
ሌላው በቦታው ላይ ርቀትን ጠብቆ ከመስተናገድ ጋር ተያይዞና ባለጉዳይ ማስክን ሳያረጉ መስተናገድ ይስተዋላል፡፡
በጉዳዩ ላይ ምላሽ የሰጡት ጠቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰአዳ አዋሌ ተቋሙን ከተረከቡ አጭር ጊዜ ቢሆናቸውም በተገልጋዩ ሚነሱ ችግሮች ፈጥነው መፍትሄ እንዲያገኙ እየሰሩ እንዳለ ተቁመው ከተገልጋይ ማረፊያና የተቀላጠፈ አገልግሎት አሰጣጥ ጋር ተያይዞ ሚስተዋለውን ችግር በፍጥነት ለመፍታት እየሰራን አእንገኛለን በቅርቡ ስትመለሱም ችግሩን አታዩትም ብለዋል፡፡
በቀጣይነት ምልከታ የተደረገው በ02ቀበሌና 09 ላይ ሲሆን በቀበሌዎቹ አገልግሎት ለማግኘት መተው ያገኘናቸው ነዋሪዎች በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ መጉላላቶች መኖራቸውን ጠቁመው በተለይ ከመታወቂያና ሌሎች አገልግሎቶች ላይ መጓተቶችና በዘመድ የመስተናገድ ችግሮች አሉ ብለዋል፡፡
ሌላው በነዚህ ቀበሌዎች ላይ አንድ ተገልጋይ ከሳምንታት በዘለለ መጉላላት አእንደሚገጥመው ምልከታ ላደረገው ቡድን ተገልጧል፡፡ የየቀበሌዎቹ የስራ ኃላፊዎችም ችግሮች መኖራቸውን አምነው አብላጫው ችግር በባለሙያ እጥረት የተከሰቱ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
ካንዳንድ ባለሙያዎች የሙያ ስነምግባር ጋር ተያይዞ ያለውን ችግር በቀጣይ እንደሚፈታ ተናግረዋል፡፡ በሌላ በኩል በድል ጮራ ሪፈራል ሆስፒታል ላይ ምልከታ የተደረገ ሲሆን በሆስፒታሉ በተለይ ከታካሚዎች ካርድ መጥፋትና ከአንዳንድ ባለሙያዎች ስነምግባር እንደሁም ከመድሀኒቶች እጥረት ጋር ተያይዞ ችግሮች መኖራቸውን ለመታዘብ ተችሏል፡፡
የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሙና በበኩላቸው ሆስፒታሉ በለውጥ ጉዞ ላይ እንዳለና የመድሀኒት እጦት ከአቅማችን በላይ ነው ብለዋል፡፡
ሰራተኛን ስነምግባር ተሞርክዞ ለተነሳው ሲመልሱ እስካሁን የደረሰን ባይርም ችግሩ ካለ ፈትሸን እንፈታለን በለዋል፡፡
ጉብኝቱን ያስተባበረው የአስተዳደሩ ፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት የመልካም አስተዳደር ዳሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ብሩክ ወርቅነህ በየተቋማቱ ገንቢ ያሉትን ሀሳብ የሰጡ ሲሆን የመንግስት ተቋማት ለህዝብ ጥቅም ቅድሚያ ሰተው በመስራት ተገልጋዩን ማርካት እንደሚጠበቅባቸው ገልፀዋል በዚህ ረገድ በህዝብ ቅሬታ የሚሰማበት ተቋም ራሱን ሊፈትሽና ችግሩን ባፋጣኝ እንዲፈታ ነው መልእክት ያስተላለፉት፡፡
የአስተዳደሩ ፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አቡበከር አብዶሽ በበኩላቸው የትኛውም ተቋም ከህዝብ በላይ እንዳልሆነ ጠቁመው በህዝቡ የተነሱትን ጥያቆዎች መሰረት በማድረግ እንደአስተዳደር ማስተካከያዎች እንዲደረጉ እንሰራለን ለአሰራር ማነቆ የሆኑ ችግሮችን እንደሰው ሀይል ሉ ችግሮች እንዲፈቱ ቢሮው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ይሰራል ብለዋል፡፡


