ቢሮው ግምታዊ ዋጋቸው 700ሺብር የሚገመቱ በትምህርት ቤቶች ውስጥ የተለያዩ የኮሮና መከላከል ስራውን የሚያግዙ የንፅህና መጠበቂያና የሙቀት ልኬት መቆጣጠሪያ ቁሳቁሶችን ለትምርት ቢሮ በድጋፍ አበርክቷል፡፡
የኮሮና ወረርሽኝ መከሰትን ተከትሎ የትምህርት ቤት ደጆች ለወራት ተዘግተው ቢቆዩም መንግስት ትምህርት ቤቶች አስፈላጊውን የኮሮና መከላከል ጥንቃቄን በማድረግ ስራቸውን እንዲከውኑ መፍቀዱን ተከትሎ ትምህርት ቤቶች ወደ እለት ተእለት ተግባራቸው ከገቡ ሰነባብተዋል፡፡
ታድያ በመማር ማስተማር ሂደት ውስጥ ኮሮናን መከላከልን መርህ ለመተግበር የግብአት እጥረት እንዳይከሰት ያግዛሉ ያላቸውን ግምታዊ ዋጋቸው 700ሺብር የሆኑ የተለያዩ የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን፤የፕላስቲክ ባልዲዎችን እንዲሁም የሙቀት ልኬት መቆጣጠሪ መሳሪያዎችን የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ በድጋፍ መልክ አበርክቷል፡፡
በስነ-ስረአቱ ላይ የአስተዳሩ ጤና ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ለምለም በዛብህ እንደተናገሩት ኮቪድ ከጊዜ ጊዜ ቁጥሩ እጨመረ መምጣቱን ጠቁመው በተለይም ትምህርት ቤቶች ላይ ተማሪዎች ለዚህ ቫይረስ ተጋላጭ እንዳይሆኑ ቢሮዋችን ከትምህርት ሴክተሩ ጋር በቅንጅት እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡
በትምህርት ቤቶች ላይ ግንዛቤን በመፍጠር እንደሁም አስፈላጊውን መከላከያ ግብአቶች በመደገፍ ዜጎች ለኮሮና እንዳጋለጡ በቀጣይም እንሰራለን የእለቱ ድጋፍም የዚሁ አንዱ ማሳያ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የድሬደዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሙሉካ በበኩላቸው እንደሀገር ትምህርት እንዲጀመር አቅጣጫ ከተሰጠበትና ወደትግበራ ከገባንበት እለት አንቶ ጤናው ሴክተር ከፍተኛ እገዛን እያደረገልን ይገኛል ብለዋል፡፡
የእለቱ ድጋፍም ለየትምህርት ቤቶቹ እንዲሰራጩ እንደሚደረግ ጠቁመው በቀጣይም እንደቢሮ ለምናደርገው የኮሮና መከላከል ተግባር ድጋፋችሁ አይለየን ብለዋል፡፡
በእለቱ በተደረገው ድጋፍም የተለያየ መጠን ያለላቸው ፈሳሽና ደረቅ ሳሙናዎች የፕላስቲክ ባልዲዎች፤የሙቀጥ ልኬት መቆጣጠሪያ መሳሪያዎች፤የማስተማሪያ ተለጣፊ ብሮሸሮች የተለያየ መጠን ያላቸው የው ማጠራቀሚያ ሮቶዎች ይገኙበታል፡፡
በዘውገ አውላችው


