በአካባቢ ልማት ስራዎች ላይ የህብረተሰብ ተሳትፎ የጎላ ድርሻ ሊኖረው እንደሚገባ ተገለፀ::

    በአስተዳደሩ የከተማ ቀበሌዎች በቀጣይ ማህበረሰቡን ያሳተፈ ዘርፈብዙ የልማት ስራዎችን ለማከናወን የሚያስችል የአደረጃጀት ፎርማት ላይ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፎሎች ለተውጣጡ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ እየተካሄደ ነው
    የድሬደዋ የህብረተሰብ ተሳትፎ እና ልማት ኤጀንሲ ዳይሬክተር አቶ ጎንፋ ሞሲሳ መንግስት በተናጠል ለህብረተሰቡ የሚያስፈልጉ ሁሉንም የልማት ስራዎች ለማሟላት የአቅምም ሆነ የገንዘብ ውስንነት እንደመኖሩ ህብረተሰቡ በአካባቢው ተጠቃሚ ሊያደርጉት የሚችሉ ስራዎችን በባለቤትነት ስሜት ማከናወን እንደሚገባው ተናግሯል::
    በቀጣይ በተለያዩ መስኮች ሁሉንም ማህበረሰብ ያሳተፈ የልማት ስራ ለማከናወን የአመለካካትና የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ኃላፊው ተናግረዋል
    በመድረኩ የተሳተፉ በበኩላቸው በአካባቢያቸው የመንገድ የመብራት እና የውሃ ልማት ስራዎችን በራሳቸው ተነሳሽነትና በነዋሪው ተሳትፎ ከመንግስት ጋር በመሆን በማከናወናቸው የነበሩባቸውን ችግሮች መቅረፍ መቻላቸውን ተናግረዋል፡፡