በውጪ ሀገራት የሚኖሩ የድሬዳዋ ልጆችና ወዳጆች ለአስተዳደሩ አንድ ሚሊዬን ብር የሚጠጋ የኮሮና ቫይረስ መመርመሪያ መሣሪያ ድጋፍ አበረከቱ፡፡

    ከዚህ ቀደም በውጪ ሀገራት የሚኖሩ የድሬዳዋ ልጆችና ወዳጆች ቃል በገቡት መሰረት ለአስተዳደራችን የኮቪድ-19 መመርመሪያ መሣሪያ በዛሬው እለት የአስተዳደሩ ከንቲባ አቶ አህመድ መሀመድ ቡህ ፣ ምክትል ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃር፣ የጤና ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ለምለም በዛብህ እንዲሁም የአስተዳደሩ ካቢኔ አባላት በተገኙበት የርክክብ ስነ-ስርዓት ተካሄዷል፡፡
    በውጪ ሀገራት የሚኖሩ የድሬዳዋ ልጆችና ወዳጆችን ወክላ ይህንን ማሽን ለአስተዳደሩ ያስረከበችው ሞደሊስት ፈቲያ መሀመድ እንደተናገረችው በውጪ የሚኖሩ የድሬዳዋ ልጆች በተለያዩ ጊዜያት ለአስተዳደሩ ያደረጉት ድጋፍ ድሬዳዋ የነበራትን ቀደምት ስሟንና የመደጋገፍ ባህላችንን ከምን ጊዜም በላይ ለማስቀጠል በሳምንት ሁለት ጊዜ በመገናኘት ስለ ድሬዳዋ እንወያያለን ብለዋል፡፡
    በተደረገው ድጋፍ ምስጋና ያቀረቡት የአስተዳደሩ ከንቲባ አቶ አህመድ መሀመድ ቡህ እንደገለፁት ከዚህ በፊት የኮሮና ቫይረስ መመርመሪያ መሣሪያ ከቅርብ ጊዜ በኋላ ከሀሮማያ ዩኒቬርስቲ የኮቪ-ድ 19 መመርመሪያ መሣሪያ በውሰት መልክ በመገኘቱ አስተዳደሩ በተፈለገው መጠን አገልግሎት መስጠት አለመቻሉን በመጠቆም ይህ ድጋፍ በመገኘቱ ህብረተሰቡ በሚፈለገው መጠን ለመመርመር ያስችለናል ብለዋል ፡፡
    በመጨረሻም በውጪ ሀገራት የሚኖሩ የድሬዳዋ ልጆችና ወዳጆች የምስጋና ምስክር ወረቀት አስተዳደሩ አበርክተዋል፡፡