በጁንታው ቡድን በህግ ማስከበርና የሀገር ህልውና በማስጠበቅ ላይ ሆነው ለተሰዉ የመከላከያ ሰራዊት አባላቶች በርክክብ ስነ ስርዐቱ የህሊና ጸሎት ተደርጓል፡፡
በስነ ስርአቱ የአስተዳደሩ ም/ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር፣ የአስተዳደሩ ፖሊስ ከሚሽን ኮሚሽነር አለሙ መግራ እንዲሁም የአስተዳደሩ ካቢኔ አባት ተገኝተዋል፡፡
በድጋፍ አሰጣጥ ስነ ስርአቱ የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ አቶ ከድር ጀሀር እንደተናገሩት የሀገራችን መከላከያ ስራዊት በትግራይ ክልል የመሸጉትን የህወሃት ቡድን ህግ ፊት ለማቅረብ ክቡር ህይወቱን እየገበረ ባለበት ባሁኑ ወቅትም የድሬደዋ አስተዳደር በገጠርና ከተማ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ማድረጉ ተጠናክሮ መቀጠሉን ጠቁመዋል።
ምክትል ከንቲባው አክለውም ከዚህ በፊትም እንደዚህ አይነቱ የሀገር ጥሪ ስመጣ የግሉ ባለሃብትና ድርጅቶች ከፊት በመሰለፍ የሀገራዊ ጥሪው ከእጥፍ በላይ ለሀገራቸውና ለህዝባቸው ሲሉ ከርመዋል አሁንም ይህንን ህገ-ወጡን ቡድን ህግ ፊት ለማቆም የሀገር መከላከያ እየወሰደ ላለው እልህ አስጨራሽ ትግል ከጎኑ መሆናችንን የምናረጋግጥበት ጊዜ ላይ እንገኛለን ብለዋል።
ባለሀብቶቹ ቃል በገቡት መሰረት በገንዘብ ከ6 ሚሊዮን ብር በላይ የደገፍ ሲሆን በቀጣይም ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል።
በድሬዳዋ አስተዳደር የሚገኙ የግል ባለሃብቶችና ድርጅቶች ለኢፌድሪ የሀገር መከላከያ ሰራዊት የብርና የአይነት ድጋፎችን አደረጉ፡፡


