የድሬዳዋ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት በአስተዳደሩ ከሚገኙ ምሁራን ጋር በብልጽግና ፓርቲ ፕሮግራም እና በምሁራን ሁለንተናዊ ሚና ዙሪያ የምክክር መድረክ አካሄደ ::

    ለድሬዳዋ አስተዳደር ምሁራን እና ከፍተኛ የመንግስት ባለሙያዎች የተዘጋጀው የምክክር መድረክ በድሬዳዋ ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መብራቴ ገብረየስ የብልጽግና አለማቀፋዊ ትርጉምና አሌመንቶች አገራት በብልጽግና እንዴት ይለካሉ፣ የብልጽግና ፓርቲ ዋና አላማዎች እና የብልጽግና ፓርቲ ፕሮግራሞች አላማን መሰረት ያደረገ የምክክር መድረክ መሆኑን ገልጸዋል።
    መድረኩ በሁለት ክፍል የተዘጋጀ ሲሆን የመጀመሪያው ክፍል ስለ ብልጽግና መሰረታዊያን ማለትም ስለ ብልጽግና ቃል አመጣጥና አለማቀፋዊ ትርጉም፣ የብልጽግና ጽንሰ ሀሳብ ሞዴል፣ የብልፅግና ምሶሶዎች አካላት እና የአገሮች የብልፅግና ደረጃ በፓርቲው አመራር ሰይፉ ታደሰ (ዶ/ር) ቀርቧል። በሁለተኛው ክፍል የብልጽግና ፓርቲ ፕሮግራም በአምስት ክፍል የብልጽግና ፓርቲ ዓላማና መለያ እሴቶች፣ የፖለቲካ ፕሮግራም፣ የኢኮኖሚ ፕሮግራም፣ ማህበራዊ ፕሮግራም እና የውጭ ግንኙነት ፕሮግራም ዘርዘር ባለ ሁኔታ የፓርቲው ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መብራቴ ገብረየስ አቅርበዋል።
    በመጨረሻም በቀረቡ ሰነዶች ሰፊ ውይይት በማድረግ ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን በማመላከት ቲንክ ታንክ ግሩፕ ለመመስረት መግባባት ላይ ለመድረስ ተችሏል።
    ምንጭ ድሬዳዋ ብልጽግና ጵ/ቤት