የአቢሲኒያ ባንክ በይቆጥቡ ይሸለሙ መርሓ ግብር የምስራቅ ኢትዮጵያ ባለዕድለኞችን ሽልማት ሰጠ
የአቢሲኒያ ባንክ “መቆጠበብ ያሸልማል ” እና “እንሸለምዎ ” በሚል መሪ ቃል በምስራቅ ኢትዮጵያ ባሉ 35 የባንኩ ቅርንጫፎች ቁጠባን መሰረት ያደረገ 15 ባለዕድለኞችን ሽልማት ሰጠ፡፡
በዚህ የሽልማት ስነ-ስርዓት ላይ የአቢሲኒያ ባንክ ድሬ ደዋ ዲስትሪክት ማናጀር አቶ ሙሉጌታ በቀለ ባደረጉት ንግግር እንደገለፁት ባንኩ ሀገራችን ለጀመረቻቸዉ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎችን በፋይናስ አቅርቦት ለማገዝና የህረተሰባችንን የቁጠባ በህል ለማሳደግ ይህ ይቆጥቡ ይሸለሙ መርሓ ግብር መጀመሩን ገልፀዉ የዛሬዉ መድረክ የመጀመሪያ ዙር ባለዕድለኞች የሽልማት ማስረከቢያ እና የሁለተኛዉ ዙር “መቆጠብ ያሸልማል ” እና “እንሸለሞዎ ” ለማስጀመር ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በመድረኩ ላይ የድሬ ደዋ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤትና የካቢኔ ጉዳዮች ምክትል ሀላፊ የሆኑት ወ/ሮ ወይንሸት ተስፋዬ ባደረጉት የመክፈቺያ ንግግር መቆጠብ ለወደፊት ዕቀዶቻችን ስኬት ካለዉ ቁልፍ ሚና በተጨማሪ የህ ሽልማት ተጨማሪ ጠቀሜታ ያለዉ በመሆኑ ሁሉም እንዲቆጥብ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡
በሌላ በኩል የድሬ ደዋ አስተዳደር የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሀላፊ አቶ እስቂያስ ታፈሰ እንዳሉት ቁጠባ የዘመናዊ አኗኗርና የዘመናዊ ህዝብ መገለጫ መሆኑን በመድረኩ ተገኝተው ባደርጉት ንግግር ገልጠዋል ፡፡ በሃገራችን የቁጠባ በሃል እጅግ አናሳ መሆኑን አስታውሰው ቁጠባን በማዳበር ረገድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አቢሲንያ ባንክ ከፍተኛ ድርሻ እየተወጣ መሆኑን አቶ እስቅያስ አብራርተዋል፡፡


